General
ሜሲ አለምን ማስገረሙን አያቆምም
TIKVAH-SPORT · 19 Oct 2026, 23:45
ኢንተር ሚያሚ ሌሊት በተደረ ጨዋታ አታላንታ ዩናይትድን 3ለ1 ሲያሸንፉ ሊዮኔል ሜሲ ሁለት ወሳኝ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
የክለቡ አሰልጣኝ ኬሊ ጎንዛሌዝ በኮከባቸው ብቃት መደናቃቸውን በገለፁበት አስተያየት “ እሱ አለምን ማስገረሙን አያቆምም “ ሲሉ ተደምጠዋል።
አሰልጣኙ አያይዘውም “ በ 39ዓመቱ የሚያደርገውን ማመን ያቅተኛል “ ሲሉ “ እሱ ደስተኛ ነው ፣ 1000 ጎሎችን እንደሚያስቆጥር በእርሱ እምነት አለኝ “ ብለዋል።
ሊዮኔል ሜሲ በመርሐ ግብሩ የጨዋታ ኮከብ በመባል መመረጥም ችሎ ነበር።
ኢንተር ሚያሚ በደረጃ ሰንጠረዡ :-
1ኛ ናሽቪል :- 6️⃣7️⃣ ነጥብ 2ኛ ኢንተር ሚያሚ :- 5️⃣5️⃣ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
