General
የማርቲኔዝ የጉዳት ሁኔታ ምን ይመስላል ?
SpoJex Desk · 20 Oct 2026, 00:48
የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ትላንት ጉዳት አጋጥሞት ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ይታወሳል።
ማርቲኔዝ በግጭቱ ምክንያት የመንጋጋ ጉዳት እንዳጋጠመው ይፋ አድርጓል።
በዚህም ምክንያት ኤሚ ማርቲኔዝ የተሳካ የመንጋጋ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉን አስታውቋል።
“ ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ” ያለው ማርቲኔዝ “ ለድጋፋችሁ አመሰግናለሁ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እመለሳለሁ " ብሏል።
ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ከጉዳቱ ቢያንስ ለአንድ ወር ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተገልጿል።
